ቀጥታ፡

በደርቢው ጨዋታ ባየር ሙኒክ ቦሩሲያ ዶርትሙንድን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 8/2018 (ኢዜአ)፦ በጀርመን ቡንድስሊጋ የሰባተኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሃ ግብር ባየር ሙኒክ ቦሩሲያ ዶርትሙንድን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ማምሻውን በአሊያንዝ አሬና ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሃሪ ኬን እና ማይክል ኦሊሴ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ጁሊያን ብራንድ ለዶርትሙንድ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። 

ውጤቱን ተከትሎ ባየር ሙኒክ በ21 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል።

በሊጉ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቦሩሲያ ዶርትሙንድ በ14 ነጥብ ከነበረበት ሁለተኛ ደረጃ ወደ አራተኛ ዝቅ ብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም