አርሰናል የሊጉን መሪነት ዳግም ተረከበ - ኢዜአ አማርኛ
አርሰናል የሊጉን መሪነት ዳግም ተረከበ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 8/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የስምንተኛ ሳምንት መርሃ ግብር አርሰናል ፉልሃምን 1 ለ 0 ተሸንፏል።
ማምሻውን በክራቫን ኮቴጅ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሊያንድሮ ትሮሳርድ በ58ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ አሳርፏል።
አርሰናል በሊጉ ከማዕዘን ምት ያስቆጠራቸው የግቦች ብዛት ሰባት አድርሷል።
በሊጉ ስድስተኛ ድሉን ያስመዘገበው አርሰናል በ19 ነጥብ የሊጉን መሪነት ከማንችስተር ሲቲ ተረክቧል።
በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ፉልሃም በስምንት ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዟል።