ቀጥታ፡

በፕሪሚየር ሊጉ ስምንተኛ ሳምንት ማንችስተር ሲቲ ኤቨርተንን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 8/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ስምንተኛ ሳምንት ማንችስተር ሲቲ ኤቨርተንን 2 ለ 0 አሸንፏል።

በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አርሊንግ ሃላንድ ሁለቱን ግቦች አስቆጥሯል።

ሃላንድ በሊጉ ያስቆጠራቸውን ግቦች ብዛት ወደ 11 ከፍ በማድረግ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን አጠናክሯል።

ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ በ16 ነጥብ ደረጃውን በጊዚያዊነት ወደ አንደኛ ከፍ አድርጓል።

በርንሌይ ሊድስ ዩናይትድን፣ ሰንደርላንድ ዎልቭስን በተመሳሳይ 2 ለ 0 አሸንፈዋል። ብራይተን ኒውካስትል ዩናይትድን 2 ለ 1 ረቷል።

ቦርንማውዝ ከክሪስታል ፓላስ ሶስት አቻ ተለያይተዋል።

ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ፉልሃም ከአርሰናል በክራቫን ኮቴጅ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም