ቀጥታ፡

ቼልሲ ኖቲንግሃም ፎረስትን በማሸነፍ ደረጃውን አሻሸለ 

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 8/2018 (ኢዜአ)፦  በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የስምንተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ቼልሲ ኖቲንግሃም ፎረስትን 3 ለ 0 አሸንፏል። 

በሲቲ ግራውንድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጆሽ አቼምፖንግ፣ ፔድሮ ኔቶ እና ሪስ ጀምስ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። 

የቼልሲው ማሎ ጉስቶ በ87ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። 

በሊጉ አራተኛ ድሉን ያስመዘገበው ቼልሲ በ14 ነጥብ ደረጃውን ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል። 

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ለአምስተኛ ጊዜ የተሸነፈው ኖቲንግሃም ፎረስት በአምስት ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም