በፕሪሚየር ሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሸገር ከተማን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በፕሪሚየር ሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሸገር ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 8/2018 (ኢዜአ)፦ በ2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አዲስ አዳጊውን ሸገር ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አብነት ተስፋዬ በ54ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
ነገሌ አርሲ ከአርባምንጭ ከተማ ከቀኑ 10 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታሉ።
በአሁኑ ሰዓት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሲዳማ ቡና በመጫወት ላይ ይገኛሉ።
ከቀኑ 9 ሰዓት እና ድሬደዋ ከተማ ከሃዋሳ ከተማ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።