የቦሩሲያ ዶርትሙንድ እና ባየር ሙኒክ የሚያደርጉት ተጠባቂ የደርቢ ጨዋታ - ኢዜአ አማርኛ
የቦሩሲያ ዶርትሙንድ እና ባየር ሙኒክ የሚያደርጉት ተጠባቂ የደርቢ ጨዋታ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 8/2018(ኢዜአ):- በጀርመን ቡንድስሊጋ የሰባተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ባየር ሙኒክ ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ ዛሬ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ጨዋታው ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ 75 ሺህ 024 ተመልካች በሚያስተናገደው አሊያንዝ አሬና ስታዲየም ይደረጋል።
ባየር ሙኒክ በሊጉ እስከ አሁን ባደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች ስድስቱንም አሸንፏል። ቡድኑ 25 ግቦችን ሲያስቆጥር ሶስት ጎሎችን አስተናግዷል።
ሙኒክ ሊጉን በ18 ነጥብ እየመራ ይገኛል።
ተጋጣሚው ቦሩሲያ ዶርትሙንድ በሊጉ ስድስት ጨዋታዎች አራት ጊዜ ሲያሸንፍ ሁለት ጊዜ አቻ ወጥቷል። ቡድኑ 12 ግቦችን ሲያስቆጥር 4 ግቦችን አስተናግዷል።
ዶርትሙንድ በ14 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
ሁለቱ የጀርመን ተቀናቃኝ ክለቦች በሁሉም ውድድሮች ሲገናኙ የአሁኑ ለ138ኛ ጊዜ ነው።
ባየር ሙኒክ 67 ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ይዟል። ቦሩሲያ ዶርትሙንድ 33 ጊዜ አሸንፏል። በቀሪው 37 ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።
ቡድኖቹ በቡንድስሊጋው 62 ጊዜ ተገናኝተው ባየር ሙኒክ 32 ጊዜ ሲያሸንፍ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ 16 ጊዜ ድል ቀንቶታል። 14 ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥተዋል።
“ዴር ክላሲከር” የሚል ስያሜ ያለው የደርቢ ጨዋታ 60 ዓመታትን ያስቆጠረ ነው።
በመልካም ወቅታዊ ብቃት ላይ የሚገኙት ሁለቱ ቡድኖች የሚያደርጉት ጨዋታ ተመጣጣኝ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።
የ45 ዓመቱ ባስቲያን ዳንከርት ተጠባቂውን ጨዋታ በዋና ዳኝነት ይመሩታል።