ቀጥታ፡

በኮምቦልቻ ከተማ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍ ተኪ ምርቶች ላይ እንዲያተኩሩ እየተደረገ ነው

ኮምቦልቻ፤ ጥቅምት 8/2018(ኢዜአ)፡-በኮምቦልቻ ከተማ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍ ተኪና የውጭ ንግድ ምርቶች ላይ እንዲያተኩሩ እየተደረገ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ገለጹ።  

የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል በኮምቦልቻ ከተማ  የአምራች  ኢንዱስትሪዎችን  የሥራ እንቅስቃሴ እየጎበኙ ነው።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መሀመድ አሚን የሱፍ በገብኝቱ ላይ እንደገለጹት፤ በከተማው የአምራች ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍ ተኪና የውጭ ንግድ ምርቶች ላይ እንዲያተኩሩ እየተሰራ ነው። 

በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ  የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ባለሃብቶች የሚገጥሟቸውን ችግሮች መፍታት መቻሉንም አንስተዋል።

በዛሬው ጉብኝት ላይ የሚሰጡ አስተያየቶችን እንደ ግብአት በመጠቀም ከተማዋን ለኢንቨስትመንት ይበልጥ ተመራጭ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራም ገልጸዋል።

በጉብኝቱ ላይ  የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ እንድሪስ አብዱን ጨምሮ  ሌሎች የፌዴራልና የክልል ሥራ  ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም