ቀጥታ፡

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኬንያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ብሄራዊ የአስክሬን ሽኝት ላይ ተገኙ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 7/2018 (ኢዜአ)፦ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኬንያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ብሄራዊ የአስክሬን ሽኝት ስነ ስርዓት ላይ ተገኙ።


 

ፕሬዝዳንት ታዬ ጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ኡቡሩ ዴኒስ፣ የኬንያ ሚኒስቴር የካቢኔ ፀሐፊ አድን ዱአሌ፣ የኬንያ ትምህርት ሚኒስቴር የካቢኔ ፀሐፊ ጁሊየስ ኦጋምባ፣ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ እና በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል።


 

የኬንያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ብሄራዊ የአስክሬን ሽኝት በናይሮቢ በንናዮ ብሄራዊ ስታዲየም እየተካሄደ ሲሆን የተለያዩ ሀገራት መሪዎችም በስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።


 

ራይላ ኦዲንጋ በህንድ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በያዝነው ሳምንት በ80 ዓመታቸው ህይወታቸው ማለፉ የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም