ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዲንሾ ሎጅ እና የጌሴ የሳርምድርን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 7/2018 (ኢዜአ)፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና የተለያዩ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች በባሌ ዞን በመገንባት ላይ ያለውን የዲንሾ ሎጅ እና ከባቢውን እንዲሁም የጌሴ የሳርምድርን ጎብኝተዋል።


 

ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምዕራብ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከ2 ሺህ ኪሎ ሜትር ስኩየር በላይ ስፋት እንዳለው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።


 

ፓርኩ በኢትዮጵያ በከፍታው ሁለተኛ ደረጃ ያለውን ተራራ ጨምሮ አስደናቂ የመልክዓ ምድር ገጽታዎችን፣ የዱር እንስሳትን፣ ደኖችን፣ የሳር ምድሮችን እና የተለያዩ የተክል አይነቶችን በመያዙ “የተለያየ አለም በአንድ ፓርክ” ተብሎ ለመጠራት የበቃ መሆኑም ተጠቁሟል።


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም