ቀጥታ፡

አገራዊ የልማት ግቦች እንዲሳኩ ገንቢ ሚናቸውን እንደሚያጠናክሩ ወጣቶች ተናገሩ

ድሬደዋ፣ ጥቅምት 6/2018(ኢዜአ)፡- አገራዊ የልማት ግቦች እንዲሳኩ ገንቢ ሚናቸውን እንደሚያጠናክሩ የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶች ተናገሩ።

በብልጽግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አዘጋጅነት ለወጣቶችና ሴቶች ክንፍ አባላት ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቋል።

"የመደመር ትውልድ ግንባታ ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ በተሰጠው ስልጠና ላይ የተሳተፉት ወጣቶቹ አንዳሉት  እንደ አገር የተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች እውን ለማድረግ  በሚደረገው ጥረት ኃላፊነታቸውን እየተወጡ  ናቸው።

አስተያየታቸውን ከሰጡ የስልጠናው ተሳታፊዎች መካከል ወጣት ረመዳን ደስታ እንዳለው፤ በድሬዳዋ አስተዳደር የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት እንዲሳኩ ሚናውን እየተወጣ  መሆኑን ገልጿል።

ባለት እውቅትና ጉልበት ለሀገር ብልጽግና መረጋገጥ የበኩሏን በማበርከት ላይ መሆኗን የገለጸችው ደግሞ ወጣት ፅዮን ውብሸት ናት።

አገራዊ ፕሮጀክቶች በታቀደው መሰረት እንዲሳኩ  የሰላም  መስፈን መሰረት በመሆኑ ለተግባራዊነቱ  የወጣቶች  የነቃ  ተሳትፎ  ወሳኝ  መሆኑ ጠቁማለች ።

ወጣት ኢብሳ አህመድ በበኩሉ የተጀመሩ ግዙፍ አገራዊ ፕሮጀክቶች በየደረጃው  የወጣቶችን የልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንደሚያሳድጉ  ተናግሯል።

በዚህም ወጣቶች  የአካባቢውን ሰላምና ልማት በማረጋገጥ ላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ  በመሳተፍ አገራዊ የብልጽግና ትልሞች እንዲሳኩ ተሳትፎውን  ለማስቀጠል ዝግጁ መሆኑን አክሏል።

በብልጽግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ሻኪር አህመድ፣ ወጣቱ በሀገር ልማት ላይ ያለውን ተሳትፎ  ለማሳደግ አስተዳደሩ ያልተቆጠበ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

ለሀገር ልማት ሰላም መሰረት በመሆኑ  ወጣቱ   ከመንግስት ጋር ተቀናጅቶ ይበልጥ መስራት አለበት ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም