ቀጥታ፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የልማት ስራዎችን በማጠናከር የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ምክር ቤቱ ሃላፊነቱን እየተወጣ ነው

ጂንካ፤ጥቅምት 6/2018 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የልማት ስራዎችን አጠናክሮ  በማስቀጠል የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ምክር ቤቱ  ሃላፊነቱን  እየተወጣ መሆኑን የክልሉ ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ ገለጹ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤቶች የጋራ ምክክር ፎረም በጂንካ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።


 

በመድረኩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የክልሉ  ምክር ቤት ዋና አፈ- ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ፤ ምክር ቤቱ አስፈፃሚውን በመደገፍ፣ በመከታተልና በመቆጣጠር የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት  ሃላፊነቱን  እየተወጣ መሆኑን አንስተዋል።

በክልሉ ሰላምን በማፅናት ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸው ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።

የህዝብን የልማትና የአገልግሎት ፍላጎት መሰረት ያደረጉ ፍትሃዊ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ አሰራሮችም እንዲጠናከሩ  ድጋፍ ማድረጉን አንስተዋል።


 

በክልሉ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ምክር ቤቱ የበኩሉን ሃላፊነት የሚወጣ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

በምክክር ፎረሙ የክልሉ ምክር-ቤት እና የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ እና ምክትል አፈ-ጉባኤዎች የተገኙ ሲሆን የዞን፣ የከተማና የሪጂዮ ፖሊሲ ከተሞች አፈ-ጉባኤዎችም ታድመዋል።

በፎረሙ የ2017 በጀት አመት አተገባበርና የ2018 የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ምክክር ይደረጋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም