ቀጥታ፡

የማኅበረሰብ ፍትሕን በማጠናከር ለህብረተሰቡ የፍትሕ ጥያቄ ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ አገልግሎቶች እየተተገበሩ ነው-የፍትሕ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 6/2018 (ኢዜአ)፡-የማኅበረሰብ ፍትሕን በማጠናከር ለህብረተሰቡ የፍትሕ ጥያቄ ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ አገልግሎቶች እየተተገበሩ መሆኑን የፍትሕ ሚኒስትር ዴኤታ ኤርሚያስ የማነብርሃን (ዶ/ር) ገለጹ።

ፍትሕ ሚኒስቴር "በኢትዮጵያ የመሠረተ ማኅበረሰብ ፍትሕ አጠቃላይ እይታ እና ወቅታዊ መረጃ" በሚል ሃሳብ ከክልል ተቋማትና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

በዚሁ ወቅት የፍትሕ ሚኒስትር ዴኤታ ኤርሚያስ የማነብርሃን (ዶ/ር) እንዳሉት፥ በኢትዮጵያ የመሠረተ የማኅበረሰብ ፍትሕን በማጠናከር ለህብረተሰቡ የፍትሕ ጥያቄ ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ አገልግሎቶች እየተተገበሩ ነው።

ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በፍትሕ ዘርፍ በተደረገው ማሻሻያ በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸው፥ለህዝቡ ቀልጣፋ፣ ተደራሽ እና ተዓማኒ የሆነ የፍትሕ ስርዓት ተደራሽ የማድረግ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከመደበኛ ፍርድ ቤት ጎን ለጎን የመሠረተ ማኅበረሰብ ፍትሕን በማጠናከር ለህብረተሰቡ የፍትሕ ጥያቄዎች ምላሽ እየተሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህም ሕዝቡ በመሠረተ ማኅበረሰብ ፍትህ አገልግሎት እንዲያገኝ ለባህላዊ የግጭት አፈታት እና ዳኝነት እውቅና እንዲሰጥ መደረጉን ገልጸዋል።

በዚህም ህዝቡ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት ሲጠቀምባቸው የቆዩ የመሠረተ ማህበረሰብ ፍትሕን የበለጠ በማጠናከር ህዝቡ በቅርበት ፍትሕ እንዲያገኝ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

በሀገሪቱ የመሠረተ የማኅበረሰብ ፍትሕን በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

ማህበረሰቡን መሰረት ያደረገ ባህላዊ ዳኝነት ግጭቶችን ከመፍታት በተጨማሪ እርቅ በመፍጠር በማህበረሰቡ መካከል ማህበራዊ መስተጋብር የበለጠ እንዲጠናከር ያደርጋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም