ቀጥታ፡

​ ለጉበት ህመም አጋላጭ መንስኤዎች ምንድን ናቸው? ​

በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት እና የጨጓራ፣ አንጀት እና ጉበት ሰብ ስፔሻሊስት ዶክተር አብዲ ባቲ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ከአጋላጭ ምክንያቶች መካከል ከታች የተጠቀሱት ዋነኞቹ ናቸው ብለዋል።

👉 እንደ ሄፓታይተስ ቢ እና ሲ ባሉ ቫይረሶች በደም፣ በመርፌ ወይም ወሊድ ወቅት የሚተላለፉ ህመሞች፤

👉 ከመጠን በላይ አልኮል መጠቀም፤

👉 ከመጠን በላይ መወፈር ፤

👉 የስኳር በሽታ፤

👉 ከእፅዋት እና የተለያዩ እህሎች (ለምሳሌ ከማሽላ እና በቆሎ) ውስጥ የሚገኙ እንደ አፍላቶክሲን ያሉ መርዛማ ንጥረ ነገሮች፤

👉 ከ40 ዓመት በላይ መሆን፣ በቤተሰብ የሚተላለፉ የጉበት በሽታዎች መኖር፣ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እና አደገኛ ልማዶች ለጉበት በሽታ ከሚያጋልጡ መንስዔዎች መካከል ናቸው።

ከእነዚህ አጋላጭ መንስዔዎች አብዛኛዎቹ ሊወገዱ የሚችሉ እንዲሁም ቀድመን በማወቅ እና በመጠንቀቅ መከላከል የሚቻሉ ናቸው ይላሉ የሕክምና ባለሙያው።

📌 ጉበትን እንዴት ማበረታታት ይቻላል?

👉 በየዕለቱ በቂ ንጹህ ውኃ በመጠጣት፤

👉 ጤናማ አመጋገብ በመከተል (እንደ ፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ጤፍ፣ ባቄላ እና ዓሣ በመመገብ)፤

👉 ከመጠን በላይ ስብን እና ስኳርን በመቀነስ፤

👉 አካላዊ እንቅስቃሴ በማዘውተር፤

👉 አልኮልን በመገደብ ወይም ጭራሽ ባለመጠቀም፤

👉 የሄፓታይተስ ክትባት በመውሰድ፤

👉 ጉዳት እንደሌላቸው ያልተረጋገጡ እፅዋትን ከመጠቀም በመቆጠብ፤

👉 መድኃኒት ከመውሰድ በፊት የጤና ባለሙያ በማማከር እንዲሁም የግል እና የምግብ ንጽህናን በመጠበቅ የጉበትን ጤንነት መጠበቅ ይቻላል ብለዋል ዶክተር አብዲ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም