ቀጥታ፡

ለልማት ሥራዎች መፋጠን ተሳትፏችንን እናጠናክራለን - ባለሀብቶች

ጋምቤላ፤ ጥቅምት 5/ 2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለተጀመሩ የልማት ሥራዎች መፋጠን ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ  በተለያዩ የንግድና የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተሰማሩ ባለሃብቶች ገለጹ።

‎በክልሉ የልማትና የንግድ እንቅስቃሴ ዙሪያ በጋምቤላ ከተማ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ተጠናቋል ።

‎ከውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች መካከል በግብርና ኢንቨስትመንት የተሰማሩት ባለሃብት አቶ ኡሞድ ኡገር እንደገለጹት በክልሉ ለተጀመሩ የኮሪደርና ሌሎች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የልማት ሥራዎች መሳካት የበኩላቸውን ተሳትፎ ለማድረግ ዝግጁ ናቸው።

‎የአቅመ ደካማ ቤቶችን መገንባትን ጨምሮ በሌሎች የልማት ስራዎች  ሲሳተፉ መቆየታቸውን የገለጹት ደግሞ በግብርና ኢንቨስትመንት የተሰማሩት አቶ ንጉስ በራ ናቸው።

በቀጣይም በክልሉ በተጀመሩ የኮሪደርና ሌሎች ስራዎች ተሳትፏቸውን ይበልጥ አጠናከረው ለመቀጠል ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። 


 

‎ሌላዋ በሆቴል ስራ የተሰማሩት ወይዘሮ አምሳለ ገብረወልድ በሰጡት አስተያየት የንግዱ ማህበረሰብ በክልሉ የሰላምና የልማት ስራዎች ተሳትፏችንን እናጠናክራለን ብለዋል ።


 

‎የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ እንዳሉት ለክልሉ ልማትና እድገት መፋጠን የባለሀብቱ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ።

የንግዱ ማህበረሰብና ባለሀብቱ በልማት ስራዎች ተሳትፏቸውን  ሊያጠናክሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም