ለክልሉ ህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራ ውጤታማነት የምክር ቤቱ የክትትልና ቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል - ኢዜአ አማርኛ
ለክልሉ ህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራ ውጤታማነት የምክር ቤቱ የክትትልና ቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል

ቴፒ፣ ጥቅምት 4/2018 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የምክር ቤቱ የክትትልና ቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት አስታወቀ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት በ3ኛ ዓመት 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በማካሄድ የአዲስ አፈ ጉባኤ ሹመትም አጽድቋል።
የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ በመሆን የተሾሙት አቶ ጌታቸው ኬኒ፤ በስራ ጊዜያቸው አስፈፃሚውን አካል የመደገፍ፣ የመከታተልና የቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚሰሩ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ለክልሉ ህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራ ውጤታማነት የምክር ቤቱ የክትትልና ቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም አረጋግጠዋል።
የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ መሰለ ከበደ፤ በበኩላቸው ምክር ቤቱ በክልሉ ብሎም እንደ ሀገር እየተከናወኑ ባሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ጥረቶች ላይ የድርሻውን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል።
በሀገሪቱ ሰላምን በማጽናት እንዲሁም ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በማጎልበት ረገድ ብዙ ስለመሰራቱ አስታውሰው በዚህ ረገድ የምክር ቤቱ ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም አረጋግጠዋል።