አቶ ሳንዶካን ደበበ የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ - ኢዜአ አማርኛ
አቶ ሳንዶካን ደበበ የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 4/2018 (ኢዜአ)፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቶ ሳንዶካን ደበበን የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርገው ሾመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ አቶ ሳንዶካን ደበበ የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርገው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 49ኛ መደበኛ ስብሰባ በኮሚሽኑ ማቋቋሚያ ደንብ ላይ በመወያየት ደንቡ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡