ቀጥታ፡

ኢትዮጵያውያን በህብረት ያሳኩት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሠንደቃችን ከፍታ ማሳያና የመቻላችን ህያው ምስክር ነው 

አሶሳ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያውያን በህብረት ያሳኩት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሠንደቃችን ከፍታ ማሳያና የመቻላችን ህያው ምስክር ነው ሲሉ  የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አስካለች አልቦሮ ገለጹ ። 

18ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን "ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ" በሚል መሪ ቃል በአሶሳ ከተማ ተከብሯል። 


 

በመርሐግብሩም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል። 

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አስካለች አልቦሮ ፤ ኢትዮጵያውያን በህብረት ያሳኩት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሠንደቃችን ከፍታ ማሳያና የመቻላችን ህያው ምስክር ነው ብለዋል። 


 

ሠንደቅ ዓላማችን የሀገር ሉዓላዊነት መገለጫ እና የጀግንነት መለያችን ነው ሲሉም ተናግረዋል። 

የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ በማስቀጠል የሀገራችንን ብልጽግና ማረጋገጥ የሁላችንም ድርሻ ነው ያሉት አፈ-ጉባኤዋ ለሠንደቅ ዓላማ ወቅቱ የሚፈልገውን መስዋዕትነት መክፈል ያስፈልጋል ብለዋል። 


 

ሠንደቅ ዓላማ የነፃነት ምልክት እና የህብረ ብሔራዊነት ማሳያ በመሆኑ ተገቢው ክብር ሊሰጠው እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም