ቀጥታ፡

የህብረ ብሄራዊ አንድነት መገለጫ የሆነውን ሰንደቅ አላማ ክብሩን ጠብቆ ማዝለቅ የሁላችንም አደራ ሊሆን ይገባል - ርእሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ 

ሀዋሳ ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- የጀግንነት የሀገር ኩራትና የህብረ ብሄራዊ አንድነት መገለጫ የሆነውን ሰንደቅ አላማ ክብሩን ጠብቆ ማዝለቅ የሁላችንም አደራ ሊሆን ይገባል ሲሉ የሲዳማ ክልል ርእሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ።

18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን "ሰንደቅ አላማችን ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት፣ለብሄራዊ አንድነታችን፣ለሉአላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ህዳሴ" በሚል መሪ ሃሳብ በሀዋሳ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።


 

በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ክልል ርእሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፤ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በጀግንነት የደምና አጥንት ዋጋ የተከፈለበት የሀገር ምልክትና የሁላችንም የክብር መገለጫ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በማንሰራራት ጉዞ ላይ ያለች ሀገር የተደመረ አቅም የሚያስፈልጋት በመሆኑ በሰንደቁ ተሰባስበን በህብረ ብሄራዊ አንድነት ለኢትዮጵያ የብልጽግና ስኬት መስራት አለብን ብለዋል።


 

የጀግንነት የሀገር ኩራትና የህብረ ብሄራዊ አንድነት መገለጫ የሆነውን ሰንደቅ አላማ ክብሩን ጠብቆ ማዝለቅ የሁላችንም አደራ ሊሆን ይገባል ሲሉም አፅዕኖት ሰጥተዋል።

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንታዬ ከበደ፤ በበኩላቸው በየአመቱ የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ስናከብር የተከፈለበትን መስዋእትነት በማሰብና ለሀገር እድገትና ማንሰራራት በመስራት መሆን አለበት ብለዋል።


 

በክብረ በአሉ ላይ የታደሙ የፖሊስ አባላትም የኢትዮጵያዊያን የጀግንነት መገለጫና የህብረ ብሄራዊ አንድነት ምልክት የሆነውን ሰንደቅ አላማ አክብረን ማስከበራችን ይቀጥላል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም