እየተስፋፋ የመጣውን እና አሳሳቢውን የኩላሊት መድከም እንዴት መከላከል ይቻላል? - ኢዜአ አማርኛ
እየተስፋፋ የመጣውን እና አሳሳቢውን የኩላሊት መድከም እንዴት መከላከል ይቻላል?

ለኩላሊት ህመም አጋላጭ መንስዔዎችን በአግባቡ ማወቅ እና ከእነዚህ ሁኔታዎች መራቅ አስፈላጊ ነው።
ስኳርና ደም ግፊትን ጨምሮ በኩላሊት ላይ ጫና የሚያሳድሩ የተለያዩ ህመሞች ያሉበት ሰው ተገቢውን ክትትልና ሕክምና ማድረግ ይጠበቅበታል።
የደም ማነስ፣ የሰውነት ድካም፣ የቆዳ ድርቀትና ማሳከክ፣ የምግብ ፍላጎት ማጣትና ማቅለሽለሽ፣ የሰውነት ዕብጠት፣ የሽንት መጠን መቀነስ ሲስተዋል ቶሎ ተገቢውን ሕክምና ማድረግ ይመከራል።
የመድኃኒት አወሳሰድን ማስተካከልና ኩላሊትን ሊጎዱ የሚችሉ መድኃኒቶችን አለመውሰድ ተገቢ ነው።
ከመጠን ያለፈ ውፍረትን ማስወገድ፤ ከደባል ሱሶችም መታቀብ የኩላሊት መድከምን ለመቀነስ ብሎም ለጤናማ ኑሮ ይበጃል።
አመጋገብን ማስተካከል (ንጽህናው የተጠበቀ፣ የተመጣጠነ፣ ቤት ውስጥ የተዘጋጀ ምግብ መመገብ) እንደሚገባም የሕክምና ባለሙያዎች ይመክራሉ።
ጨው፣ ቅባት፣ የሥጋ ውጤቶች፣ የወተት ተዋጽዖና የታሸጉ ምግቦችን አጠቃቀም መቀነስ አስፈላጊ መሆኑም ይነሳል።