ቀጥታ፡

በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የሰለጠኑ ወጣቶች  ከራሳቸው አልፈው ሀገራቸውን እየጠቀሙ ነው- ከንቲባ ከድር ጁሃር 

ድሬደዋ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፦ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በርካታ ወጣቶች እየሰለጠኑ እና ከራሳቸው አልፈው ሀገራቸውንም እየጠቀሙ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ገለጹ።

በድሬዳዋ የሚገኙት የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ እና የኢትዮ -ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠኗቸውን ወጣቶች አስመርቀዋል።


 

በዚሁ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር፤ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከቴክኖሎጂ እና ዘመናዊ አሠራር ጋር በማስተሳሰር ለወጣቶች የአዳዲስ ስራ ፈጠራ አቅም መሆናቸውን ገልጸዋል።

አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን በመስራት ከራሳቸው አልፈው በርካቶች ለሀገር ለውጥና የዕድገት እንቅስቃሴዎች የላቀ አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆኑንም አንስተዋል።


 

ለቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በተሰጠው ትኩረት ወጣቶች እየሰለጠኑና እየሰሩ ከራሳቸው አልፈው ሀገራቸውን እየጠቀሙ ይገኛሉ ብለዋል።

በመሆኑም ተመራቂዎች በሰለጠኑበት ሙያ ፈጠራቸውንና ብቃታቸውን በመጠቀም ለለውጥ እንዲተጉ ከንቲባው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ሮቤል ጌታቸው፤ በአስተዳደሩ ክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራን በላቀ ጥራት ለማሳካት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ወጣቶች በቀሰሙት ዕውቀት ለራሳቸውና ለከተማቸው ለውጥ እንዲሰሩ አስገንዝበዋል።


 

በድሬዳዋ፤ የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ እና የኢትዮ -ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ከደረጃ አንድ እስከ አምስት ያሰለጠኗቸውን 1 ሺህ 42 ወጣቶችን ነው ያስመረቁት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም