የሀዋሳ ከተማ ምክር ቤት የከንቲባ ተክሌ ጆንባን ሹመት አፀደቀ - ኢዜአ አማርኛ
የሀዋሳ ከተማ ምክር ቤት የከንቲባ ተክሌ ጆንባን ሹመት አፀደቀ

ሀዋሳ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፦ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማዋን ከንቲባ ተክሌ ጆንባን ሹመት አጽድቋል።
የሀዋሳ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 10ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።
ምክር ቤቱ በጉባኤው የቀረበለትን የከተማዋን ከንቲባ ተክሌ ጆንባን ሹመት ተቀብሎ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
አቶ ተክሌ ጆንባ ከወረዳ እስከ ክልል በተለያዩ የሥራ ዘርፎች በኃላፊነት ሲመሩ መቆየታቸውም በወቅቱ ተጠቅሷል።
አዲሱ ከንቲባ ተክሌ ጆንባ በጉባኤው ፊት የተሰጣቸውን የህዝብና የመንግስት ኃላፊነት በታማኝነትና በቅንነት ለመወጣት ቃለ መሀላ የፈፀሙ ሲሆን ከቀድሞው ከንቲባ መኩሪያ ማርሻዬ የኃላፊነት ርክክብ አድርገዋል።