የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የመክፈቻ ንግግርን አስመልክቶ የቀረበውን የድጋፍ ሞሽን አዳመጡ - ኢዜአ አማርኛ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የመክፈቻ ንግግርን አስመልክቶ የቀረበውን የድጋፍ ሞሽን አዳመጡ

አዲስ አበበ፤መስከረም 29/2018(ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ለሁለቱ ምክር ቤቶች ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበውን የድጋፍ ሞሽን አድምጧል።
6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአምስተኛ ዓመት የስራ ዘመን አንደኛ መደበኛ ስብሰባው በሁለት አጀንዳዎች ላይ ውይይት አካሂዷል።
በዚህም ምክር ቤቱ በመጀመሪያ አጀንዳው በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለ ጉባኤን መርምሮ በማጽደቅ ስብሰባውን ጀምሯል።
በመቀጠልም በአንደኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ መስከረም 26/2018 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መደበኛ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበን የድጋፍ ሞሽን አዳምጧል።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጂጌ(ዶ/ር) የድጋፍ ሞሽኑን አቅርበዋል።
በመጨረሻም የምክር ቤቱ አባላት ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ መስከረም 26/2018 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መደበኛ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ በቀረበው የድጋፍ ሞሽን ላይ ተወያይተዋል።