የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ተግባራትን የመከታተል እና የመደገፉ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል- ምክር ቤቱ - ኢዜአ አማርኛ
የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ተግባራትን የመከታተል እና የመደገፉ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል- ምክር ቤቱ

ወላይታ ሶዶ፤መስከረም 29/2018 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተያዘው ዓመት የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ የክትትል እና የድጋፍ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ምክር ቤት አስታወቀ።
የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን መደበኛ ጉባኤውን በነገው ዕለት በአርባ ምንጭ ከተማ ያካሄዳል።
የምክር ቤቱ ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ እንደገለጹት ምክር ቤቱ በክልሉ የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ የሚከናወኑ ተግባራት እንዲጠናከሩ እየሰራ ነው ።
በየደረጃው የህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲኖራቸውና እየታዩ ያሉ ለውጦች እንዲጠናከሩ ምክር ቤቱ የተጣለበትን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
ጉባኤው በህዝብ ዘንድ የሚነሱ ቀሪ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመመለስ የሚያግዙ አቅጣጫዎች የሚቀመጡበት እንደሆነም ተናግረዋል።