ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሳይፕረስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሳይፕረስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 28/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሳይፕረስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኮንስታንቲኖስ ኮምቦስ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ከተመለሱ በኋላ የሳይፕረስ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኮንስታንቲኖስ ኮምቦስ እና የልዑካን ቡድናቸውን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን ገልጸዋል።
ሁለቱ ሀገራት የዲፕሎማቲክ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ብሎም ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ትብብራቸውን ለማጎልበት ጠንካራ ፍላጎት እንዳላቸው አመልክተዋል።
በመሆኑም እነዚህን የጋራ አላማዎች ለማራመድ የሚጠቅሙ ሰፊ አድማስ ያላቸው ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ተናግረዋል።