ቀጥታ፡

አቶ ኢሳያስ ጅራ የፊፋ የፀረ-ዘረኝነት እና ፀረ-አግላይነት ኮሚቴ አባል ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 28/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና የካፍ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ኢሳያስ ጅራ የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) የፀረ-ዘረኝነት እና ፀረ-አግላይነት ኮሚቴ አባል ሆነው መመረጣቸውን ፌዴሬሽኑ አስታወቀ። 

አቶ ኢሳያስ በኮሚቴው ለአራት ዓመት (እ.አ.አ ከ 2025 እስከ 2029)  እንደሚያገለግሉ አመልክቷል። 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በፕሬዝዳንቱ ሹመት የተሰማውን ደስታ ገልጾ መልካም የሥራ ዘመን ተመኝቷል። 

በተያያዘም የጋና እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ከርት ኤድዊን ሳይመን-ኦክራኩ የኮሚቴው ሊቀ መንበር ሆነው ተመርጠዋል። 

የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) የፀረ-ዘረኝነት እና ፀረ-አግላይነት ኮሚቴ በዓለም እግር ኳስ ዘረኝነትን እና ሁሉንም አይነት አግላይነትን ለመዋጋት የሚያወጣቸውን ስትራቴጂካዊ ኢኒሺቲቮች እና ሪፎርሞች ተፈጻሚ እንዲሆኑ የሚሰራ ነው።

በዚህም ኮሚቴው በእግር ኳሱ ከታዳጊ ጀምሮ እስከ ፕሮፌሽናል እርከን እኩልነት፣ አካታች እና መከባበር እንዲሰፍን የማድረግ ተግባራትን ያከናውናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም