ቀጥታ፡

ከተማ አስተዳደሩ አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የጀመራቸውን ተግባራት አጠናክሮ ቀጥሏል -ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 28/2018 (ኢዜአ)፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የጀመራቸውን ተግባራት አጠናክሮ መቀጠሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የቦሌ ቅርንጫፍ በዛሬው ዕለት ተመርቆ ወደ ሥራ ገብቷል።

በምረቃው ሥነ-ሥርዓት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር)፣ የብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።


 

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ በአስተዳደሩ ውስጥ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማቀላጠፍ ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት እየተሠራ ነው።

የአስተዳደሩን የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ቀልጣፋ ለማድረግ በቁርጠኝነት መስራታችንን ቀጥለናል ብለዋል።

የአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት የቦሌ ቅርንጫፍ የአስተዳደሩን አገልግሎት አሰጣጥ በእጅጉ በማዘመንና የዜጎችን እንግልት በመቀነስ የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግሩን ለማፋጠን ያግዛል ብለዋል።

ማዕከሉ የዲጂታል ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት የተሟላለት በመሆኑ ከሌብነትና ብልሹ አሰራር የጸዳ አገልግሎት መስጠት ያስችላል ነው ያሉት።

ቀደም ሲል የነበረውን የተንዛዛ አሰራር በማቅለል ማህበረሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ ያደርጋል ሲሉም ከንቲባዋ ተናግረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የጀመራቸውን ተግባራት አጠናክሮ መቀጠሉንም ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም