ቀጥታ፡

በጋራ ግልጽ፣ተጠያቂነት የሰፈነባት እና የበለጸገች ሀገር እንገነባለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2018 (ኢዜአ)፡-በጋራ ግልጽ፣ተጠያቂነት የሰፈነባት እና የበለጸገች ሀገር እንገነባለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ የ7ኛው የታማኝ ግብር ከፋይ እውቅና ሥነሥርዓት ተሸላሚዎችን እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ጠቁመዋል።


 

ባለፈው ዓመት የምታዋጡት ግብር ለጋራ እድገት እና ለሕዝባዊ ጠቀሜታ በሚውሉ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ እንደሚውል ቃል ገብተን ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ዛሬ በከተማችን ኮሪደሮች የሚታየው ለውጥ ለዚያ ቃላችን ሕያው ምስክር ሆኖ ይታያል ብለዋል።

አስታውሱ፣የዛሬ ጥረታችሁ የነገን ትውልድ የተሻለ መፃኢ እድል እየቀረፀ ነው በማለትም ገልጸዋል።

ሙስናን እና ሌብነትን ለማስወገድ በምናደርገው ጥረት ሥርዓቶቻችንን ማጠናከራችንን እንቀጥላለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ግብር ከፋዮችም በመሰል ጎጂ ተግባር የተሠማሩ ሰዎችን ባለመተባበር እንዲያግዙ አሳስበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በጋራ ግልጽ፣ተጠያቂነት የሰፈነባት እና የበለጸገች ሀገር እንገነባለን ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም