የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሀገር ኢኮኖሚ ከሚያበረክተው ትልቅ አስተዋጽኦ ባሻገር ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በሚገባ እየተወጣ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሀገር ኢኮኖሚ ከሚያበረክተው ትልቅ አስተዋጽኦ ባሻገር ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በሚገባ እየተወጣ ነው
አዲስ አበባ፤ መስከረም 26/2018(ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሀገር ኢኮኖሚ ከሚያበረክተው የጎላ አስተዋጽኦ ባሻገር ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በሚገባ እየተወጣ ነው ሲሉ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ገለጹ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ28 ሺ ኪሎ ግራም በላይ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የተደረገው ድጋፍ በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍል የሚገኙና ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን በተለይም ሴቶችን እና ህፃናትን ለማገዝ ትልቅ አቅም ይሆናል።
የአንድ ሀገር ዕድገት የሚለካው በመሰረተ ልማትና በኢኮኖሚ ዕድገት ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ አገልግሎትን በማስፋፋት መሆኑን ጠቅሰው፤ የአየር መንገዱ ተግባር የዚህ ማሳያ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሀገር ኢኮኖሚ ከሚያበረክተው ትልቅ አስተዋጽኦ ባሻገር ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በሚገባ እየተወጣ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ሥራ ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለማ ያደቻ፤አየር መንገዱ ከ28 ሺ ኪሎ ግራም በላይ የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።
ድጋፉ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች ተደራሽ እንደሚሆን አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያውያን ችግር በኢትዮጵያውያን የሚፈታበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ያሉት አቶ ለማ፤ አየር መንገዱ ድጋፋን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።