ባህርዳር እንደ መስከረም ንጋት ውበት፣ ተስፋ እና ልማት ሆኖላት ተመልክተናል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
ባህርዳር እንደ መስከረም ንጋት ውበት፣ ተስፋ እና ልማት ሆኖላት ተመልክተናል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 26/2018(ኢዜአ)፦ ባህርዳር እንደ መስከረም ንጋት ውበት፣ ተስፋ እና ልማት ሆኖላት ተመልክተናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው በሰፈሩት መልዕክት ውሃ ከነውበት እና ስክነቱ፤ መልክዓ ምድር ከነ ለምነቱ፤ ልምላሜ ከነ ንጹህነቱ የታደለችው የውበት ምልክቷ ባህርዳር በጠንካራ አመራርና ነዋሪዎች የጋራ ጥረት ውበቷ ይበልጥ እየፈካ እና እየደመቀች ነው ብለዋል።
በግዙፉ ዓባይ ላይ የተገነባው ባለግርማው ድልድይ ለባህርዳር ከድልድይም በላይ መለያ ቀለሟ፣ የቱሪዝም መዳረሻዋ መሆኑን ተመልክተናል ነው ያሉት።
ባህርዳር ውበቷን እና ክብሯን የሚመጥኑ የመናፈሻ ስፍራዎች እየተገነቡ፤ የኮሪደር ልማቱም ከውበት የተሻገረ ልማት አሳላጭ ሆኖ በፍጥነት እና ፈጠራ እሴቶች እያማረች ነው ብለዋል፡፡
የብልጽግና ጉዟችን መዳረሻም እንደሃገር ወደሚመጥነን ከፍታ መሸጋገር ነው ሲሉም አክለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በመልዕክታቸው።