የፍትህ ስርዓቱን ለማዘመን የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ- ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ - ኢዜአ አማርኛ
የፍትህ ስርዓቱን ለማዘመን የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ- ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 26/2018(ኢዜአ)፡-መንግስት የፍትህ ስርዓቱን ለማዘመን የጀመራቸው ተግባራቶችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ።
6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ መንግስት የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ሰላምና እድገትን የሚያረጋግጡ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ነው።
ከዚህ ውስጥም የዜጎች ዋስትንና ለማረጋገጥ የፍትሕ ስርዓቱን ለማዘመን የጀመራቸውን ተግባራት አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።
በተለይም የፍትሕ ተቋማትን አሰራር የማዘመን እና በዘርፉ ላይ ያሉ ማነቆዎችን የመፍታት ስራ በስፋት የሚሰራ እንደሆነም አመልክተዋል።
በተያዘው አዲስ ዓመትም በሀገሪቱ የተሻሻሉ የወንጀልና የፍታብሔር ህጎች በቴክኖሎጂ እንዲደገፉ የማድረግ ስራም እንደዚሁ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን አንስተዋል።
ባህላዊ የፍትህ ስርዓቶች የሚኖራቸውን አስተዋጽኦ አሟጦ ለመጠቀም እንዲቻልም በአሰራር እንዲደገፍ የማድረግ ስራ በልዩ ትኩረት የሚከናወን ይሆናል ነው ያሉት።