ሰባተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ተዓማኒ ይሆን ዘንድ መንግስት በኃላፊነት ይሰራል - ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ - ኢዜአ አማርኛ
ሰባተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ተዓማኒ ይሆን ዘንድ መንግስት በኃላፊነት ይሰራል - ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 26/2018(ኢዜአ)፡-ሰባተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ተዓማኒ ይሆን ዘንድ መንግስት በኃላፊነት እንደሚሰራ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ አስታወቁ፡፡
ስድስተኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አምስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ- ሥርዓት ተካሂዷል፡፡
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ በዚሁ ወቅት ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፤ በተያዘው በጀት ዓመት የሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ውጤታማ እንዲሆን መንግስት ይሰራል ብለዋል፡፡
ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ተዓማኒ ይሆን ዘንድ መንግስት በኃላፊነት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
መላው ህዝብ ኢትዮጵያ ያቀደቻቸው እና የጀመረቻቸውን ግዙፍ የለውጥ እርምጃዎች አበርትቶ እንዲደግፍ እና በትጋት እንዲሳተፍ ጥሪም አቅርበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ወዳጆች እና አጋሮችም ከኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ጎን እንዲቆሙ እና ለስኬቱ ሁነኛ አጋር እንዲሆኑም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
መልካም የስኬትና የተግባር ዓመት እንዲሆንም ተመኝተዋል፡፡