ከሥርዓት መለዋወጥ ጋር የማይናዱ ተቋማት ለመፍጠር የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ - ኢዜአ አማርኛ
ከሥርዓት መለዋወጥ ጋር የማይናዱ ተቋማት ለመፍጠር የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 26/2018(ኢዜአ)፡- ከሥርዓት መለዋወጥ ጋር ማይናዱ ነጻ፣ ገለልተኛ እና ሕዝባዊ ብሔራዊ ተቋማት ለመፍጠር መንግሥት ጽኑ መሠረት በመጣል ላይ እንደሚገኝ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ።
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤት 5ኛው የሥራ ዘመን የ2018 የጋራ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የ2018 የመንግስት ዋና ዋና የልማት ዕቅዶችን የተመለከተ ንግግር እያደረጉ ነው።
በንግግራቸውም፤ ከሥርዓት መለዋወጥ ጋር የማይናዱ ነጻ፣ ገለልተኛ እና ሕዝባዊ ብሔራዊ ተቋማት ለመፍጠር መንግሥት ጽኑ መሠረት በመጣል ላይ ይገኛል፤ ይህ አሠራር በ2018ም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
አንድነታችንንና ሰላማችንን በማይናወጥ ደረጃ ላይ ለማድረስ መንግሥት በተቋማት ግንባታ ላይ አበክሮ ይሠራል ብለዋል።
ብሔራዊ የጸጥታና የደኅንነት ተቋማት የሥርዓት ለውጥን የሚሻገሩ እና የሀገርን ቀጣይነት የሚያረጋግጡ ብርቱ ተቋማት እንዲሆኑ መንግሥት በቁርጠኝነት ይተጋል ነው ያሉት።