ቀጥታ፡

መንግስት የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቶችን የሚጠግን የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሞች ውጤት እያስገኙ ናቸው -ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 26/2018(ኢዜአ) ፡- መንግስት የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቶችን የሚጠግን የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሞች ውጤት እያስገኙ እንደሚገኙ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ ።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል።

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የመክፈቻ ንግግር እያደረጉ ናቸው።

በአዲሱ ዓመት መባቻ የበርካታ ዓመት ቁጭት የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መመረቁ እና በመስከረም ወር መባቻ የከርሰ ምድር ሀብታችን የሆነው የተፈጥሮ ጋዝ መውጣቱ የኢትዮጵያ እድገት መልህቅ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።

መንግስት የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቶችን የሚጠግን የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሞች ውጤት እያስገኙ እንደሚገኙም አመልክተዋል።

ከነጠላ ወደ ብዝሃነት የኢኮኖሚ ልማት በመሸጋገር እየተከናወኑ ባሉ ስራዎች የኢትዮጵያ ኤክስፖርት እያደገ እና ኢኮኖሚው ተጨባጭ ለውጥ እያሳየ ይገኛል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም