ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ የኃይል አማራጭ ልማት መጠናከር ለፈጣን ሀገራዊ እድገትና ማንሰራራት ፋይዳው የላቀ ነው - ምሁራን

ሀዋሳ፤ መስከረም 26/2017 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ የኃይል አማራጭ ልማት መጠናከር ለፈጣን ሀገራዊ እድገትና ማንሰራራት ፋይዳው የላቀ መሆኑ ተገለጸ።

በዚህ ጉዳይ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተመራማሪዎች፤ የኢትዮጵያ የኃይል አማራጭ ልማት መጠናከር ለፈጣን ሀገራዊ እድገትና ማንሰራራት ፋይዳው የላቀ መሆኑን አብራርተዋል።

በዩኒቨርሲቲው የፖሊሲ ልማትና ምርምር ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ተስፋዬ ሰመላ፤ የኢትዮጵያ የኃይል ልማት አማራጭ እየሰፋና እያደገ መምጣቱ ከሀገርም ባለፈ ለቀጣናው እድገት ወሳኝ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

የዩኒቨርሲቲው ምርምርና ትብብር ምክትል ፕሬዚዳንት ታፈሰ ማቲዮስ (ዶ/ር)፤ አንድ ዓይነት ብቻ የኃይል አጠቃቀም  መከተል ሃገራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለውን ጥረት ሊያዘገየው ስለሚችል ተጨማሪ የኃይል አመራጮችን ወደ ስራ ማስገባቱ ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።


 

በዩኒቨርሲቲው መምህርና ተመራማሪው ምህረተአብ አብርሀም (ዶ/ር) በበኩላቸው ኢትዮጵያ ተግባራዊ እያደረገቻቸው ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የግል ባለሀብቱን በተለያዩ መስኮች ኢንቨስት እንዲያደርግ የሚያነሳሱ ናቸው ብለዋል።


 

የእነዚህ ፕሮጀክቶች እውን መሆን መንግስት የግል ባለሃብቶችን በይበልጥ በመሳብ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ስራዎች ላይ እንዲሰማሩ የሚያነሳሳ መሆኑን አመልክተዋል።

ከዚህ ባለፈም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ዘርፉን ለማሳደግ የራሱን አዎንታዊ ሚና ሊጫወት እንደሚችልም አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም