የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፤ መስከረም 26/2018(ኢዜአ)፦ 6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል።
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአንድ ዓመት የሥራ ጊዜ ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ መሆኑ ተደንግጓል፡፡
በዚህ መሰረትም የ6ኛው ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የተጠናቀቀ ሲሆን 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በተገኙበት በዛሬው ዕለት ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡
ፕሬዝዳንት ታዬ ለሁለቱ ምክር ቤቶች ዓመታዊ ሥራቸውን እንደጀመሩ በማብሰር የፌዴራል መንግስቱን ዓመታዊ ዕቅድም ያቀርባሉ፡፡