ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የልማት ስራዎችን ለመጎብኘት ባህርዳር ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የልማት ስራዎችን ለመጎብኘት ባህርዳር ገቡ
አዲስ አበባ ፤መስከረም 25/ 2018 (ኢዜአ)፦ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የክልሉን የልማት ስራዎች ለመጎብኘት ባህርዳር ከተማ ገብተዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ተፈጥሮ በውሃ፣ በልምላሜ እና በዘንባባ በኳላት ውብ ምድር ባህርዳር ገብተናል ብለዋል።
በቆይታቸውም የአማራ ክልል ፖሊስ የሪፎርም ሥራ፣ የዲጂታላይዜሽን ማብሰሪያና አዲስ ህንፃን እንደሚያስመርቁ አስታውቀዋል።
በተጨማሪም በፈጠራ እና ፍጥነት እሳቤ በተቃኘ ልማት ላይ የምትገኘውን ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎች ተዘዋውረው እንደሚመለከቱ ጠቁመዋል።
በባህርዳር ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሞቀ አቀባበል ላደረጉላቸው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እና ካቢኒያቸው እና የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል::