የሆረ ሀርሰዴ ኢሬቻ በዓል ምስጋና የማቅረብ ሥነ-ሥርዓት ተጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የሆረ ሀርሰዴ ኢሬቻ በዓል ምስጋና የማቅረብ ሥነ-ሥርዓት ተጀመረ
ቢሾፍቱ ፤መስከረም 25/2018 (ኢዜአ)፦የሆረ ሀርሰዴ ኢሬቻ በዓል ምስጋና የማቅረብ ሥነ-ሥርዓት ተጀመረ ።
የሆረ ሀርሰዴ ኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ በመከበር ላይ ይገኛል።
በበዓሉ ላይ አባ ገዳዎች፣ሀደ ሲንቄዎች እና የበዓሉ ታዳሚዎች እየተሳተፉ የሚገኝ ሲሆን ስነ ስርዓቱም በአባ ገዳዎች ምርቃት ተጀምሯል::
የበዓሉ ታዳሚዎችም ባህላዊ እሴቱን ተከትለው ስርዓቱን እያከናወኑ ነው።
ኢሬቻ የኦሮሞ የገዳ ስርዓት መገለጫ ከሆኑት ውስጥ አንዱ ሲሆን፥ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ በተለያዩ ቦታዎች በስፋት የሚከበር የባህልና እሴት መገለጫ የምስጋና በዓል ነው።
የዘንድሮው ኢሬቻ በዓል “ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል ነው እየተከበረ ያለው።
ከሌሊት ጀምሮ በመከበር ላይ ባለው የሆረ ሀርሰዴ ላይ በርካቶች ታድመውበታል።