ቀጥታ፡

በተጠባቂው የሊጉ ጨዋታ ቼልሲ  ሊቨርፑልን አሸነፈ  

አዲስ አበባ፤ መስከረም 24/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሰባተኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሃ ግብር ቼልሲ ሊቨርፑልን  2 ለ 1 አሸንፏል። 

ማምሻውን በስታንፎርድ ብሪጅ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሞሰስ ካይሴዶ በ14ኛው ደቂቃ በግሩም ሁኔታ ባስቆጠረው ግብ ቼልሲ መሪ ሆኗል።

ከእረፍት መልስ ኮዲ ጋፕኮ በ63ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ጎል ሊቨርፑልን አቻ አድርጋለች።

እስቴቫኦ ዊሊያን በ96ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል ለቼልሲ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አስገኝታለች። 

ውጤቱን ተከትሎ ሊቨርፑል በ15 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ቡድኑ ዳግም የሊጉ መሪ የመሆን እድሉን ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

ሊቨርፑል በሊጉ ተከታታይ ሽንፈት አስተናግዷል።  ቼልሲ በ11 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።  

አርሰናል በ16 ነጥብ አዲሱ የሊጉ መሪ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም