አርሰናል ዌስትሃም ዩናይትድን በማሸነፍ የሊጉ መሪ ሆኗል - ኢዜአ አማርኛ
አርሰናል ዌስትሃም ዩናይትድን በማሸነፍ የሊጉ መሪ ሆኗል
አዲስ አበባ፤ መስከረም 24/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሰባተኛ ሳምንት መርሃ ግብር አርሰናል ዌስትሃም ዩናይትድን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዴክላን ራይስ በጨዋታ እና ቡካዮ ሳካ በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
በሊጉ አምስተኛ ድሉን ያስመዘገበው አርሰናል በ16 ነጥብ የሊጉን መሪነት ከሊቨርፑል በጊዜያዊነት ተረክቧል።
በውድድር ዓመቱ ለአምስተኛ ጊዜ የተሸነፈው ዌስትሃም ዩናይትድ በአራት ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
በሌላኛው የሊጉ መርሃ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ በሜሰን ማውንት እና ቤንጃሚን ሼሽኮ ግቦች ሰንደርላንድን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ውጤቱ በጫና ላይ ለሚገኙት የዩናይትድ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም እፎይታን የሰጠ ሆኗል።
ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ቼልሲ እና ሊቨርፑል በስታምፎርድ ብሪጅ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።