ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት የሴቶች፣ የወጣቶችና አካል ጉዳተኞች ተሳትፎ ወሳኝ ነው-ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ - ኢዜአ አማርኛ
ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት የሴቶች፣ የወጣቶችና አካል ጉዳተኞች ተሳትፎ ወሳኝ ነው-ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
ጅግጅጋ ፤ መስከረም 24/2018 (ኢዜአ):- ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት የሴቶች፣ የወጣቶችና አካል ጉዳተኞች ተሳትፎ ወሳኝ እንደሆነ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ገለፁ።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሶማሌ ክልል ለሴቶች፣ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኛ የማህበረሰብ ክፍሎች ያዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫና የምክክር መድረክ በጅግጅጋ ከተማ ዛሬ ተጀምሯል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ እንዳሉት፤ ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት የሴቶች፣ የወጣቶችና አካል ጉዳተኞች ተሳትፎ ወሳኝ ነው።
የአገራዊ ምክክሩ ሂደት ያለ ሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኛ ማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፎ እውን ሊሆን አይችልም ብለዋል።
በዚህም መሰረት ኮሚሽኑ የእነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን ዋና ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩም በክልሉ የሚገኙ እነዚሁ የህብረተሰብ ክፍሎች በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ላይ ግንዛቤ የሚያገኙበትና ምክረ ሀሳብ የሚሰጡበት ነው ብለዋል።
የውይይት መድረኩም "የሴቶች፣ የወጣቶች እና የአካል ጉዳተኞች ሚና ለውጤታማ ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ" በሚል መሪ ሀሳብ በጅግጅጋ ከተማ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል።
በመድረኩም የኮሚሽኑ አመራሮችን ጨምሮ ከተለያዩ የክልሉ ወረዳዎች የተውጣጡ ወጣቶች፣ ሴቶች እና አካል ጉዳተኛ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።