የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣መስከረም 24/2018(ኢዜአ):- የዘንድሮው የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው።
በበዓሉ ላይ ለመታደም ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በባህላዊ አልባሳት አጊጠው ወደ አዲስ አበባ የተጓዙ በርካታ ሰዎች በዓሉ ወደሚከበርበት ወደ ኢሬቻ ፓርክ እያቀኑ ይገኛል።
በበዓሉ አከባበር ላይ አባ ገዳዎች፣ አባ መልካዎች፣ አባ ሙዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎችና ወጣቶችን ጨምሮ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ታድመዋል፡፡
የበዓሉ ታዳሚዎችም የኦሮሞ ሕዝብን ባህል በሚያንጸባርቁ አልባሳትና ጭፈራዎች ታጅበው በድምቀት እያከበሩ ይገኛሉ።
የኦሮሞ ገዳ ስርዓት አንድ አካል እና መገለጫ የሆነው የኢሬቻ በዓል እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት እየተከበረ ነው።
የ2018 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል "ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት" በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ ነው።