ቀጥታ፡

በሶማሌ ክልል የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ

ጅግጅጋ ፤ መስከረም 20/2018 (ኢዜአ)፡-በሶማሌ ክልል የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ የሴቶች እና ህጻናት ቢሮ ገለጸ። 

ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት በሶማሌ ክልል ሴቶች እና ህጻናት ቢሮ የሴቶች አቅም ማብቃት ዳይሬክተር ወይዘሮ ዘሃራ አብዲ እንዳሉት፣ በክልሉ የሴቶች ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ባለፉት ዓመታት ሴቶች በሀገሪቷ እየተከናወኑ ላሉ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ የልማት ዘርፎች ውጤታማነት አበርክቶዋቸው የጎላ መሆኑን አንስተው፥ በተለይም በማህበራዊ ተሳትፎና በሰላም ግንባታ ሂደቶች ላይ የጎላ ሚና እንደነበራቸው ገልጸዋል።

በዚህም በክልሉ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማጠናከር እየተከናወኑ ያሉ ጥረቶች ይበልጥ እንደሚጠናከሩ አስገንዝበዋል።

በክልሉ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በመከላከልና የሴቶችን አቅም በመገንባት ረገድ እየተከናወኑ ባሉ ተግባራት ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን አንስተው፤ ይህንን ለማጠናከር የግንዛቤ ማሳደጊያ ሥራዎች ይሰራሉ ብለዋል።

ሴቶች በሥራ ፈጠራ፣ በብድርና ቁጠባ እንዲሁም በሌሎችም የልማት መስኮች ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ በተሰሩ ስራዎች ስኬቶች እየተመዘገቡ እንደሚገኙም ተናግረዋል። 

በበጀት ዓመቱ ከ35 ሺህ በላይ ሴቶችን በሥራ እድል ፈጠራ ተጠቃሚ ለማድረግ ከክልሉ የክህሎትና ሥራ ፈጠራ ቢሮና ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ጋር በትብብር እየተሠራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በለውጡ ዓመታት የክልሉ ሴቶች በአመራርነት፣ በውሳኔ ሰጭነትና በሌሎችም የልማት መስኮች ያላቸው ተሳትፎና ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱን ገልፀው፤ ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም