የኢትዮጵያ ዋንጫ ጥቅምት 9 ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዋንጫ ጥቅምት 9 ይጀመራል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 20/2018 (ኢዜአ)፦ የ2018 የኢትዮጵያ ዋንጫ ጥቅምት 9 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
ከጥቅምት 9 እስከ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በሚደረገው የአንደኛ ዙር ውድድር የከፍተኛ ሊግ ተሳታፊ ቡድኖች ይሳተፋሉ።
ቡድኖቹ የዙር ውድድር በሚያካሂዱበት ከተማ በየምድባቸው የእርስ በርስ ጨዋታ በማድረግ አሸናፊ ቡድኖች በሁለተኛው ዙር ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቡድኖች ጋር በመቀላቀል እንደሚጫወቱ ፌዴሬሽኑ አመልክቷል።
ወላይታ ድቻ የወቅቱ የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ነው።