ማዕከላዊ ዕዝ የሚሰጡትን ግዳጆች በብቃት በመወጣት ጀግንነቱን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል - ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ - ኢዜአ አማርኛ
ማዕከላዊ ዕዝ የሚሰጡትን ግዳጆች በብቃት በመወጣት ጀግንነቱን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል - ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2018(ኢዜአ)፡-የሀገር መከላከያ ሰራዊት ማዕከላዊ ዕዝ የሚሰጡትን ግዳጆች በብቃት በመወጣት ጀግንነቱን በተግባር እያረጋገጠ እንደሚገኝ የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ ገለጹ፡፡
በማዕከላዊ ዕዝ ሥር የሚገኘው 103ኛ ጊቤ ኮር አራተኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ይገኛል።
በበዓሉ ላይ የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ፣ የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሠረት፣ የሪፐብሊካን ጥበቃ ኃይል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ ረጋሳ፣ የ103ኛ ጊቤ ኮር አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ጀማል ከድር፣ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ በዚሁ ወቅት፤ ማዕከላዊ ዕዝ የሚሰጡትን ግዳጆች በብቃት በመወጣት ጀግንነቱን በተግባር እያረጋገጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ማዕከላዊ ዕዝ ተቋሙ የሚሰጠውን ግዳጅ ከማከናወኑም በላይ እራሱን እንደንስር እያደሰ አስተማማኝ ዕዝ መሆን ችሏል ነው ያሉት።
የ103ኛ ጊቤ ኮር የተሰጠውን ተልዕኮ በጀግንነት በመወጣት አኩሪ ገድል እየፈጸመ ይገኛል ብለዋል።