አርሰናል ኒውካስትል ዩናይትድን በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አገኘ - ኢዜአ አማርኛ
አርሰናል ኒውካስትል ዩናይትድን በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አገኘ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 18/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሃ ግብር አርሰናል ኒውካስትል ዩናይትድን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በሴይንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጀርመናዊው አጥቂ ኒክ ዎልትሜድ በ34ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ጎል ኒውካስትል መሪ መሆን ችሏል።
ሚኬል ሜሪኖ በ84ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፈው ጎል አርሰናልን አቻ አድርጓል።
በ97ኛው ደቂቃ ጋብርኤል ማጋሌስ ከመረብ ላይ ያሳረፈው ጎል አርሰናልን አሸናፊ ሆኗል።
ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል በ13 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ከሊጉ መሪ ሊቨርፑል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ዝቅ አድርጓል።
ኒውካስትል ዩናይትድ በስድስት ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ቀን ላይ በተደረገ ጨዋታ አስቶንቪላ ፋልሃምን 3 ለ 1 በማሸነፍ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አግኝቷል።