ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ መድን የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን ከዛንዚባሩ ምላንዴጌ ጋር ዛሬ ያካሂዳል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 17/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ መድን የ2025/26 የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን ከዛንዚባሩ ምላንዴጌ ጋር ዛሬ ያደርጋል። 

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ከቀኑ 10 ሰዓት ከ15 በአማኒ ስታዲየም ይካሄዳል። 

ኢትዮጵያ መድን በአበበ በቂላ ስታዲየም ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ በአማኑኤል ኤርቦ እና ብሩክ ሙሉጌታ ግቦች 2 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።  

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ መድን ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ እድሉን አስፍቷል።

መድን በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ በመጨረሻው ዙር ከሩዋንዳው ኤፒአር እና ከግብጹ ኤፍሲ ፒራሚድስ አሸናፊ ጋር ይጫወታል።

ኢትዮጵያ መድን የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ እየተወዳደረ ይገኛል።  

በገብረመድህን ኃይሌ የሚሰለጥነው ቡድን በውድድሩ ላይ ሲሳተፍ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም