ወላይታ ድቻ ከካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር ውጪ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
ወላይታ ድቻ ከካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር ውጪ ሆነ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 17/2018 (ኢዜአ)፦ ወላይታ ድቻ በ2025/26 የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የማጣሪያ የመልስ ጨዋታ በሊቢያው አል-ኢትሃድ 3 ለ 1 ተሸንፏል።
ትናንት ማምሻውን በትሪፖሊ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ናኡፌል ዜርሁኒ፣ ታታያኦኔ ዲትልሆክዌ እና አህመድ አል ቢዚ አስቆጥረዋል።
ቴዎድሮስ ታፈሰ ለወላይታ ድቻ ብቸኛዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ውጤቱን ተከትሎ አል-ኢትሃድ በድምሩ 3 ለ 1 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።
አል-ኢትሃድ በመጨረሻው ዙር ከግብጹ አል ማስሪ ጋር ይጫወታል።
የወላይታ ድቻ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጉዞ በመጀመሪያው ዙር ተገቷል።
ወላይታ ድቻ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን ወክሎ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ ነው።