የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የመስቀል በዓልን በተለያዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓቶች እያከበረች ትገኛለች - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የመስቀል በዓልን በተለያዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓቶች እያከበረች ትገኛለች
አዲስ አበባ፤ መስከረም 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የ2018 የመስቀል በዓልን በተለያዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓቶች በላዛሪስት ገዳም ጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያን እያከበረች ትገኛለች።
በበዓሉ የሃይማኖት አባቶች እና የእምነቱ ተከታዮች የታደሙበት ሲሆን የተለያዩ መንፈሳዊ ዝማሪዎች እና የወንጌል ስብከቶችም እየቀረቡ ይገኛሉ።