በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የመስቀል ደመራ በዓል እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የመስቀል ደመራ በዓል እየተከበረ ነው
ባሕር ዳር፤ መስከረም 16/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የመስቀል ደመራ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው።
በዓሉ እየተከበረ ያለው በባህር ዳር፣ በደሴ፣ በደብረ ብርሃን፣ በደብረ ማርቆስ፣ በወልዲያና በሌሎች የክልሉ ከተሞች እንዲሁም በተለያዩ የገጠር አካባቢዎች መሆኑ ተመላክቷል።
በየአካባቢው በዓሉ እየተከበረ ያለው በርካታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሃይማኖት ተከታዮች፣ የእምነቱ አባቶች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ነው።
በደመራ በዓል ማክበሪያ ስፍራ የምስጋና ወረብ ከቀረበና ለምዕመናን ትምህርት ከተሰጠ በኋላ በጋራ ደመራ የመለኮስ ሥነ ስርአት ማምሻውን ይከናወናል።
በጎንደር፣ በላል ይበላ፣ በሰቆጣና በሌሎች የሰሜኑ አካባቢ በሚገኙ ከተሞችም የመስቀል ደመራውን ዛሬ ምሽት በመደመር በነገው እለት ጧት ረፋድ ላይ የሚለኮስ ሥነስርት እንደሚከናወን ታውቋል።