ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 16/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በተለያዩ ዘርፎች ላይ አጠቃላይ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
እነዚህም የኃይል ማመንጫ፣ ግብርና፣ የጤና ጥበቃ ልማት እና የመከላከያ ትብብርን ያካትታሉ ብለዋል።
በተለይም ለማኅበረሰብ አገልግሎት የሚውል ንፁህ ኃይል ለማቅረብ የጋራ የኒኩሊየር ኃይል ማመንጫ ለማልማት ስምምነቶችን በመፈራረም የጋራ ፍላጎቶቻችንን የሚያጎለብቱ ጉዳዮች ላይ ተማክረናል ሲሉ ገልጸዋል።